“የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ ዕድገት!!” ሀገራዊ ስልጠና አካል የሆነው በኣሪ ዞን ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
በነበረው ስልጠና አመራሩ የተሻለ አካባቢያዊ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን እንዲገነዘቡ ተጠማሪ ግንዛቤን መፈጠሩን የኣሪ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ ገልፀዋል።
በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን እንደምቹ አጋጋሚ በመጠቀም ሰፋፊ ልማቶችን ሕዝቡን በማቀናጀት ተግባራዊ ማድረግ የሰልጠኝ አመራር ቁልፍ ተግባር መሆን እንዳለበት አቶ ጉራልቅ አሳስበዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ የነበረው ስልጠና የአመራሩ ክህሎት፣ ብቃትና ዕውቀቱ ከተግባር ጋር ተሰናስኖ መምራት የሚያስችል መልዕክት መተላለፉን አብራርተዋል።
ዛሬ ለነገ ለውጥ መነሻ በመሆኑ ነገን የተሻለች ዞን፣ ክልል ብሎም ሀገር ለማየት በቁርጠኝነትና በቁጭት አመራሩ በአንድ አሀድና አስተሳሰብ መሥራት ይጠበቅበታል ሲሉም አቶ አብርሃም አሳስበዋል።
በስልጠናው በነበራቸው ቆይታ ወጥ የሆነ ሀገራዊ አንድነትና እሳቤ ኖሮን የመምራት አቅማችንን እንዲናሳድግ ግንዛቤ መጨበጣቸውን ሰልጣኝ አመራሮች ገልፀዋል።
ይህንን ወደ ተግባር ለመቀየር የተሰጠንን ሀላፊነት ለመወጣት እንሠራለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ስልጠናው በተሳካ መልኩ መልዕክት ተላልፎ የተቋጨ ሲሆን በቀጣይ የርዕሰ ጉዳይ ሐሳቡ በተዋረድ 4ኛና 5ኛ ዙር ድረስ እንደሚወርድም ታውቋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በማህበረሰቡ ውስጥ የተለመዱና የተዛቡ የስርዓተ ጾታ አመለካከቶችን ለመቅረፍ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ