በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት” በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በደንባ ጎፋ ወረዳ የዛንጋ ዶርማለ የወተት ላም እና የዙሉዚ ጺላ የፊዬል ማሞከት የተደራጁ ማህበራት የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የእስፔ ዲቻ ህብረት ስራ ዩኒየን የመኖ ማቀነባበሪያ ጎብኝተዋል።
ሰልጠኝ አመራሮች በመስክ ምልከታ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው በቁርጠኝነት መሥራት ከተቻለ ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ገልፀዋል።
የመስክ ምልከታዉ ሰልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ከተግባር ተሞክሮና ከልምድ መማማር የሚያስችል ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን የደንባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ ገልጸዋል።
የጎፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ያዕቆብ ሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው እንደሀገር የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የመስክ ምልከታው አቅም እንደሚፈጥርላቸው ጠቁመዋል።
ዘጋቢ ፡ አይናለም ሰለሞን-ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ