የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ አመራሮች በሶዶ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
“የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል ርዕስ በአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ያሉ አመራሮች በሶዶ ከተማ የተሰሩ የተለያዩ ልማት ስራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሰልጣኞች በሶዶ ከተማ የሌማት ትሩፋትና በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ነው የጎበኙት።
ሠልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ልምድ ልውውጥ ማድረግ ፋይዳዉ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተመላክቷል።
“የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል ሀሳብ በወላይታ ዞን በየደረጃው የሚገኙ 1 ሺህ 5 መቶ የሚጠጉ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ከተማ ስልጠናውን እየወሰዱ መሆናቸውን ይታወሳል።
ዘጋቢ ፡ በቀሌች ጌቾ -ከዋካ ቅርንጫፍ

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ