ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ
በጎፋ ዞን ከጥቅምት 23 ጀምሮ በፈታ ካፕ ለሚሳተፉ ስምንት የጤና ቡድኖች የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ በተበረከተበት ወቅት የሳውላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እርቦላ እርኮ በከተማዋ ጤና ስፖርት ቡድኖች መስፋፋታቸው ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ ማህበራዊ ትስስር በማጎልበት ጤናማ አምራች እና ሰላማዊ ዜጋን ለመፍጠር ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
የፈታ ካፕ አስተባባሪና የድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አዳነ ተካ በበኩላቸው፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአራት ከተሞች በሚገኙ ቡድኖች ከ8 መቶ በላይ ስፖርተኞች በፈታ ካፕ እንደሚሳተፉ ገልጸው ለአሸናፊ ቡድኖች የተለያዩ ማበረታቻ ሽልማቶች ማዘጋጀታቸውን አስረድተዋል፡፡
የጤና ቡድን አባላቱ ለአካባቢያቸው ብሎም ለከተማዋ የስፖርት እድገት ከፈታ ጋር በጋራ ለመስራት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀው በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል።
የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታደለ ታደሰ በበኩላቸው፤ ፈታ ካፕ በዞኑ ከሚገኙ የጤና ቡድኖች መካከል ለስምንቱ ቡድኖች ስላደረገው ድጋፍ አመስግነው ማህበረሰቡ በጤና ስፖርት እንዲሳተፋ በዞኑ በትከረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ንቁ፣ ብቁ፣ ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመምሪያው የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ቡድን መሪ አቶ ትኩ ተላይነህ ሕብረተሰቡ በግልም ሆነ በጤና ቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማዘውተር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከመከላከል ባሻገር ወንድማማችነትን የሚያጎለብት በመሆኑ የሁልጊዜ ተግባር ሊያደርጉት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የጤና ቡድን አባላት በበኩላቸው በጤና ስፖርት በመሳተፍ የጤና ጥቅሞች ማግኘታቸውን ተናግረው ለከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት፣ ልማት እና ሰላም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ