ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦችን አንድነት በሚያጎላ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የከምባታ ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አስካለ ሰሶ ገለጹ
የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶችም ተግባሩን በበላይነት የመምራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በ1987 ዓ.ም የኢፌዲሪ ህገ መንግስት የጸደቀበትን ቀን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ይከበራል።
የዘንድሮ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከሌሎች ዓመታት በተለየ ሁኔታ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ስራውን እያከናወነ ባለበት ወቅት የሚከበር መሆኑን የተናገሩት የከምባታ ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለ ሰሶ፤ በዓሉም በህዝቦች መካከል አንድነትን በሚያጎላ መልኩ እንዲከበር በዞን ደረጃ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዓሉ በዞን ደረጃ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች እና በቀበሌያት ደረጃ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።
ቀኑን ምክንያት በማድረግም ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ የውይይት መድረኮች እንደሚዘጋጁ ወ/ሮ አስካለ አስረድተዋል።
በዓሉ በታቀደው መልኩ እንዲከበር ሁሉም ህብረተሰብ የድርሻውን ሊያበረክት ይገባል ሲሉም አጉባኤዋ አሳስበዋል።
የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤቶችም ተግባሩን በበላይነት የመምራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ወ/ሮ አስካለ ጠቅሰዋል።
በአርባምንጭ ከተማ በሚከበረው በዓል ላይ የዞኑ የባህል ኪነት ቡድን የብሔረሰቡን ማንነት የሚገልጹ ትዕይንቶችን ይዛዉ እንደሚቀርቡና ይህም የእርስ በርስ መቀራረብን ለማጠናከር መልካም ዕድል እንደሆነም ተናግረዋል።
የዘንድሮ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ ይከበራል።
ዘጋቢ: ተሻለ ከበደ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለፁ
እንደሀገር ካለንበት ችግሮች ወጥተን ዜጎች ተረጋግተው የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን ምክክሩ እንደሚያግዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ
የጂንካ ዩኒቨርስቲ ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ