በክልሉ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና ክፍተቾችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና ክፍተቾችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ገለፀ።

ቢሮው በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በክልሉ በትራንስፖርት እና በመንገድ ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ዙሪያ ወደ ዞንና ልዩ ወረዳዎች ለድጋፍና ክትትል ከሚሰማሩ የቢሮው ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የመሠረተ ልማት ክላስተር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አማን ኑረዲን በዚሁ ወቅት እንዳሉት ቢሮው በትራንስፖርትና በመንገድ ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና ክፍተቾችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት መገምገሙንና ይህንን መነሻ በማድረግም ለቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች ተግባራቱ ያሉበትን ደረጃ ወደ ዞንና ልዩ ወረዳ በመውረድ ክትትል እንዲያደርጉ ስምሪት መሰጠቱን በመጠቆም የመስክ ምልከታው ዋና ዓላማም በዘርፉ ያሉ ጠንካራ ጎኖችንና መሻሻል ያለባቸው ተግባራትን በመለየት ለቀጣይ ስራ በግብዓትነት ለመጠቀም ያለመ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በሁለቱም ዘርፎች የሚሰማሩ አካላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸው የጠቆሙት አቶ አማን፤ የዞንና ልዩ ወረዳ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት የድርሻቸውን ሊወጡ እንሚገባ አሳበዋል።

የክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሰምበቶ አባባ በበኩላቸው በትራንስፖርትና በመንገድ ልማት ዘርፍ የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻነት የዕቅዱ ፊዚካልና ፋይናንሻል አፈጻጸሙ በታችኛው መዋቅር ያለበት ደረጃ የሚከታተል ቡድን መሠማራቱን አስረድተዋል።

ምልከታው ቢሮው በቀጣይ ከአፈፃፀም አንጻር በጥንካሬ የሚወሰዱና መሻሻል ያለባቸውን ተግባራትን በመለየት ቢሮው የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ዕድል እንደሚፈጥር አመላክተዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ መሀመድ ኤከሶ፣ ቅባቱ በረዳና በሰጡት አስተያየት መድረኩ በመስክ ምልከታው ወቅት በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥና ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ጋር ተያይዞ ችግር የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

ዘጋቢ፡ መሐመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን