ከ1 ሺህ 8 መቶ በላይ ሥራ-አጥ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው ወደ ሥራ መግባታቸውም ተጠቁሟል።
ወጣት ሚታ ኦሎሎ፣ ከፋይ ካሣየ እና ወጣት በላቸው በሽር በዞኑ የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ከሪበላ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ከዚህ በፊት ሥራ በማጣት የቤተሰብ ጥገኛ በመሆን መቸገራቸውን ተናግረው አሁን ላይ በማህበር በመደራጀት በተደረገላቸው ድጋፍ ወይፈን በማደለብ ሥራ ላይ ተሰማርተው በመስራት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በወረዳው ሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ንግድና ገበያ ልማት አደራጅ ባለሙያ የሆኑት አቶ አፋንጎ ወጆሮ ሥራ-አጥ ወጣቶችን በመለየት በማህበር በማደራጀት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች መሰማራታቸውንና ውጤታማነታቸውንም በየጊዜው ድጋፍና ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በዞኑ የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ማጆሬ በበኩላቸው በወረዳው በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 8 መቶ 32 ሥራ-አጥ ወጣቶችን በመለየት በፍላጎታቸው መሠረት በ21 ኢንተርፕራይዞች በማደራጀት ወደ ሥራ ማሰማራት መቻሉን አብራርተዋል።
በዚህም መንግስት ለሥራ ዕድል በሰጠው ትኩረት መነሻ በወይፈን ማደለብ፣ ፍየልና በግ በማሞከት፣ የዶሮ ጫጩት በማርባትና መሰል የሥራ መስኮች በማስገባት ወጣቶቹ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
በቀጣይም ሥራ አጥነትን የመቀነስ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አስረድተዋል።
ወጣቶቹም የተገኘውን ስራ ሳይንቁ ሰርተው እራሳቸውንና አካባቢያቸውን መለወጥ እንዳለባቸው አቶ ግርማ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: ደረጀ ተፈራ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለፁ
እንደሀገር ካለንበት ችግሮች ወጥተን ዜጎች ተረጋግተው የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን ምክክሩ እንደሚያግዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ
የጂንካ ዩኒቨርስቲ ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ