ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ የሚገኝ መረጃ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ
ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ የሚገኝ መረጃ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ካነጋገርናቸው በዞኑ አመያ ከተማ የ01 ቀበሌና የጨካ ቦቻ ነዋሪዎች መካከል አቶ ታጋይ ዶነቾ እና ሙላቱ መሸሻ፤ ወሳኝ ኩነት የአንድን ግለሰብ አጠቃላይ ሁኔታን የሚይዝ መሆኑን በማንሳት የግለሰብ ከልደት እስከ ሞት ያለውን ሙሉ ማስረጃ እንደሚይዝና ይህንን በመመዝገብ መረጃ በመያዛቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለሰዉ ልጆች ታሪክ መነሻዎቹ የክስተቶቹ ቦታ ወይም አገር ሆኖ ከጊዜያት፣ ቀናት፣ ወራት፣ ዓመታት እና ዘመናት መነሻ መሰረቶቹ በተፈጥሮአዊ ክስተት የተወለዱበት ልደት ቀን እና ከተወለዱበት ጀምሮ ኖረው የሞቱበት ጊዜያት እንዲሁም በማህበረሰባዊ ክስተቶች ሁለቱም ጥንዶች መቼ እንደተጋቡ፣ በጋብቻቸዉ ባጋጠማቸዉ አለመግባባት ፍቺ መቼ እንደተፈፀመ እና የራስ ያልሆነዉን ልጅ እንደራስ ልጅ ለማሳደግ ጉዲፈቻ የተፈፀመበትን ክስተት መፈራረቅ ቀኖችን በወሳኝ ኩነቶች በምዝገባ አስመዝግበዉ ህጋዊ የእዉቅና ሠነድ መያዝ አገር አቀፋዊ የዜግነት ጉዳይ በመሆኑ በዚህም ተመዝግበው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዞኑ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስተባባሪ ወ/ሮ ዘውዲቱ እንዳለ፤ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተለያዩ የሀገሪቱን ፖሊስ እና እቅዶችን ለማዘጋጀት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ግንባታ የሚገኘውን መረጃ ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ህግና ለተለያዩ መሠረተ ልማት አገልግሎት እንዲውል በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነትን ማጠናከር ወሳኝነት አለዉ ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህም የተነሳ የተፈጥሮም ሆነ ማህበረሰባዊ ክስተቶችን በዜጎች ምዝገባ መዝገብ ላይ በማስመዝገብ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መብቶችን በፍትሀዊነት መጠቀም እንዲቻል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ምስክር ወረቀት መያዝ ዘመናዊነት ስለሆነ የሚከሰቱ ኩነቶችን በአቅራቢያው በሚገኙበት ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ከሚሠሩበት ተቋም የሠራተኛነት መታወቂያ ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር በመያዝ በክብር መዝገብ ሹም (ሥራ አስኪያጅ) አማካይነት በወቅቱ ማስመዝገብ ዘመናዊነት ነው ብሎዋል።
የዞኑ ሠላም፣ ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ እስራኤል ጮንቄ በበኩላቸው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ በተለይ መንግስት የሚያወጣቸውን ጥቅል ዕቅዶችና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ለትምህርት የደረሱ ህፃናት በትክክለኛ ዕድሜ በትምህርት ዓመቱ እንዲመዘገቡ ለማድረግና መመዝገባቸውን ለመከታተል፣ በየአቅራቢያው ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት አገልግሎት ተቋማት የህጻናትን ዝርዝር መረጃ ከልደት ምዝገባ መነሻ በማድረግ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ስንቶቹ እየተማሩ ናቸው? ስንቶቹስ ከትምህርት ዉጭ ናቸዉ? የሚለዉን መለየት የሚቻልበት መንገድ ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚገኘው መረጃ መሆኑም ጠቁመዋል።
ዜጎችን ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በሚሰጠዉ ሰርተፍኬት በትምህርትም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ዉጭ አገር ለመዉጣት ወይም ከዉጭ አገር ለመመለስ ወይም ወደ ሌላ አገር ዜግነትን ለመጠየቅ ያለወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መረጃ እንደማይቻል ዜጎች ተረድቶ በዞኑ ብሎም በክልሉ ልደት እስከ 90 ቀናት ዉስጥ፣ ሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ጉዲፈቻ እና ሌሎችንም እስከ 30 ቀናት ዉስጥ በመመዝገብ ወይም በማስመዝገብ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሰርተፍኬት የመያዝ ባህል ሊኖር ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ፋሲካ ሙሉጌታ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የመማር ማስተማር ሂደቱ የተሻለ ቢሆንም የትምህርት ግብአት እጥረት እንዳሳሰባቸው አንዳንድ ተማሪዎች ገለጹ
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ