የምስራቅ ጉራጌ ዞን አሰተዳደር በስልጤ ዞን በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመጠለያ ግንባታ የሚሆን 1 ሚሊየን ብር የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ
በዚሁ ወቅት የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች የኛም ወገኖች ናቸው፤ ጉዳታቸው ጉዳታችን ነው ብሎ ለቤት ግንባታ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ላደረገው የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ድጋፉ በስልጤ ዞን በጎርፍ ለተጉዱ ወገኖች በአራት መኪና ለቤት ግንባታ የሚሆን ፍልጥ፣ ማገርና ተሸጋጋሪ የሚሆን ቁሳቁስ ነው ብለዋል።
ወንድማዊና ጎሮቤታዊ ፍቅራችንን ለመግለፅ ጅምር ድጋፍ ነው ያሉት አቶ ሙስጠፋ አብሮነታችንን በማጠናከርና ሰው ሰራሽም ይሆን የተፈጥሮ ችግሮች ሲያጋጥሙን በጋራ ለመካፈል ማሳያ ነው ብለዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን የጎረቤት ህዝብ ከተጎጂዎች ጎን በመሆን የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ሁሉ በቀጣይም ያደርጋል ብለዋል።
ምንጭ፡ የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!