የሸኮ ከተማ አስተዳደር በመደራጀቱ የተለያዩ መንግስታዊ አገለግሎቶችን በአቅራቢያ ማገኘታቸው እንዳስደሰታቸው የከተማው ነዋሪዎች ገለፁ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ)የሸኮ ከተማ አስተዳደር በመደራጀቱ የተለያዩ መንግስታዊ አገለግሎቶችን በአቅራቢያ ማገኘታቸው እንዳስደሰታቸው የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ዜጎች ፈጣንና ቃልጣፋ አገለግሎት አገኝተው የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አስታውቀዋል።
በከተማ አደረጃጀት መዋቅር በፈረጅ 3 የተደራጀችውን የሸኮ ከተማ ወደተሻለ ደረጃ ለማድርስ ተቀናጅተው እንደሚሰሩም የሸኮ ወርዳ ዋና አስተዳዳሪ አስታውቋል።
ካነጋገርናቸው የሸኮ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በወርዳ ውስጥ በነበረ ጊዜ ረጅም ጊዜ ይወስድ እንደነበረና አሁን ራሱን ችሎ ከተማው ሲደራጅ በወርዳ ላይ የነበረ ጫና ከመቀነሱም ባለፈ በአቅራቢያቸው እየተገለገሉ እንደሚገኙም ገልፀዋል።
የሸኮ ከተማ አስተዳደር እንደሌሎች ያደጉት ከተማ ተረታ እንዲሰለፍ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንደሚወጡም የከተማው ነዋሪዎችም ተናገርዋል።
የሸኮ ከተማ አስተዳደር መደራጀቱ የዘመናት የህዝቡ የመልማት ጥያቄ ከመሆኑም ባለፈ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የፖለቲካዊ አገለግሎቶችን በአቅራቢያ እንዲያገኙ ያስቻለ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የከንቲባው ተወካይ አቶ ንጉሴ ዱዳብ ገልፀዋል።
የከተማ አስተዳደር መዋቅር ከተደራጀ በኃላ የተለያዩ ተቋማት አገለግሎትን እንዲሰጡ ከማደረግ ባሻገር በከተማ ውስጥ ያሉትን መሬቶች በአግባቡ ማስተዳደር መቻሉንም የከንቲባው ተወካይ ጠቁመዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩን የተሻለና ለከተማው ነዋሪ ተገቢውን አገለግሎት ለመስጠት ኃላፊነት የተሰጣቸው የአመራር አካላት ተግቶ እየሰሩ እንደሚገኙ አቶ ንጉሴ አውስተው የአገለግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም አሰረድተዋል።
የሸኮ ከተማ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደራጅ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥተው በመሥራት ተግባራዊ ማደረጉን የሸኮ ወርዳ ዋና አስተዳደር አቶ አሪ ጉርሙ አመስግነው የከተማው መዋቅር መፈጠሩ ወርዳ ላይ የነበርውን ከፍተኛ የሥራ ጫና በመቀነስ የከተማ ነዋሪው አገለግሎት እንዲያገኝ አስችሏል ብለዋል።
ከተማ እያደገ ሲመጣ የህብረተሰቡ የልማት ፍላጎትም እያደገ እንደሚሄድ እና በፈርጅ 3 የተደራጀችው የሸኮ ከተማ ለማሳደግ ወረዳውም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ዋና አስተዳደሪው ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ