ማህበረሰቡ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ምርት ሊያመርቱ እንደሚገባ ተጠቆመ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሌማት ትሩፋት እና የ30 40 30 እሳቤዎችን በመተግበር ውጤታማ መሆናቸዉን በደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በዘርፉ የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ችግሮችን በመቅረፍ የአካባቢዉ ማህበረሰብና የተቋማት ተወካዮች የሚፈጠርላቸዉን ግንዛቤ ወደ መሬት ያወረዱ በመሆኑ ተጠቃሚ እየሆኑ ነዉ።
ወጣት ፈለቀ ፋኩ አርብቶ አደር ሜሪ ሙሌ፤ አባይነህ ሊራሶ እና ሌሎች እንደገለፁት በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በንብ ማነብ ዘርፍ በተዘረጉ የልማት ፕሮጀክቶች በመሣተፍ ተጠቃሚ እየሆኑ ነዉ።
የወረዳዉ ግብርና ጽ/ቤት የሰብል ኤክስቴንሽን ዘርፍ እና የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ጌትነት ከበደ፤ የአካባቢዉን ማህበረሰብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየተሠሩ ባሉ ስራዎች አበረታች ዉጤቶች እየተመዘገበ መሆኑን አመላክተዋል።
ሃላፊዉ አያይዘዉም በወረዳው የአካባቢዉ ማህበረሰብ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታዎች ተጠቅመዉ ከዚህ በላይ አልምተው መጠቀም የሚችሉበት ሰፊ መሬትና በቂ የውሃ አማራጭ እንዳለ ጠቅሰዉ በተያዘው የምርት ዘመን በግብርናዉ ዘርፍ እንደ ወረዳ 5 ሺ 6 መቶ ሄክታር እየለማ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ወንድማገኝ በቀለ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ህዝቡን የሚለውጡ ልማቶችን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ
በነዳጅ ምርቶች ስርጭት ላይ የሚታየውን ሕገ ወጥ አሠራር ለማረም በትኩረት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ
ባላፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ