ሀዋሳ፡ ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በህዝቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንደሚሰራ የዳውሮ ዞን የስራ ሀላፊዎች ገለጹ፡፡
ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ የዋካ ኢሠራ መንገድ ተበላሽቶ ለሳምንታት ያህል ዝግ ሊሆን መቻሉ ተመላክቷል።
ህብረተሰቡ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ጫና መጋለጡን የጠቆሙት የዞኑ የሥራ ሃላፊዎች ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ጠቁመው፥ ችግሩ በታየበት አካባቢ በአካል ተገኝተው የመንገድ ጥገናና ከፈታ ስራ ማስጀመራቸው ተመላክቷል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡን የሥራ ሃላፊዎች መካከል አቶ ባቲሳ በተላ እና አቶ አንድነት ቡንጉዶ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግርና አንገብጋቢ ጉዳይ ለይቶ በመፍታትና ያጋጠመውን የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህ የመንገድ ጥገና ስራ በዝናብ ወቅት ተበላሽቶ አገልግሎት ሳይሰጥ ለሳምንታት የቆየውን መንገድ ዳግም ስራ ማስጀመር ላይ ትኩረት መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡
የዳውሮ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አስፋው መሸሻ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባውን የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አመላክተው፥ የዋካ ኢሠራ መንገድ ብልሽት ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ያስከተለ በመሆኑ፥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሰርቶ ለችግሩ እልባት ለመስጠት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ አፈወርቅ ኦሹ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ሀገራዊ ምክክር፤ የመደማመጥ፣ የመግባባትና የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት ነው!
ከ23 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ተገለጸ
በግንቦት እና ሰኔ 2018 ዓ.ም ወራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ፣ በቱሪዝም፣ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በሀገር በቀል ሪፎርም እና ቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።