ባህር ዛፍ በባህሪው ከረጅም ጊዜ በኋላ ለአገልግሎት የሚደርስና የመሬት ለምነትንም የሚያጠፋ በመሆኑ ከእርሻ ማሳቸው እያስወገዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
የወረዳው አርሶአደሮች በአጭር ጊዜ ምርት ከሚሰጡ የጓሮ አትክልቶችና ሰብሎች የሚያገኙትን ጥቅም በማነፃፀር አስረድተዋል፡፡
የደቡብ ኣሪ ወረዳ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዮሐንስ ማምሶ በበኩላቸው የወረዳው አርሶአደሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ከማሳቸው የባህርዛፍ ተክልን በማስወገድ በተለያዩ የጓሮ አትክልትና ሰብሎች እየሸፈኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ሀላፊው አያይዘውም የባህር ዛፍ ተክል ለተለያዩ አገልግሎቶች ጠቃሚ በመሆኑ ለተክሉ አመቺ በሆኑና በተመረጡ ስፍራዎች ማልማት እንደሚቻል አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ዳኜ ጥላሁን – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!