ደም በመለገስ የሌሎችን ህይወት ለመታደግ በመቻላቸው ከፍተኛ የህሊና እርካታ እንደተሰማቸው በታርጫ ከተማ ያነጋገርናቸው ደም ለጋሾች ገለጹ
በዳውሮ ዞን የታርጫ ደም ባንክ የደም ለጋሾችን ብዛት ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በታርጫ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደም ሲለግሱ አግኝተን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች በደም እጥረት የሚሰቃዩ እናቶችና ታካሚ ማህበረሰቦችን ህይወት ለመታደግ በተለያዩ ጊዜያት ልገሳ እንደሚያደርጉ ገልጸው በዚህም ከፍተኛ ደስታና እርካታ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የታርጫ ደም ባንክ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዙፋን አየል ተቋሙ በዳውሮና ኮንታ ዞኖች ላሉ 4 ሆስፒታሎች አገልግሎት እየሰጠ እንዳለ ገልፀዋል።
ፈቃደኛ የሆነ የደም ለጋሾችን መጠን ለማሳደግ የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተሠሩ በመሆናቸው አሁን ላይ የለጋሾች ቁጥር እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።
የደም ባንኩ በ2017 3 ሺህ የደም ከረጢት ለሆስፒታሎች ለማቅረብ አቅዶ እየሠራበት ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ