የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማስተማር አገልግሎት እና ለዘመናዊ እንስሳት እርባታ አገልግሎት የሚውል የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ግዥ መፈፀሙን አስታውቋል፡፡
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ስነ-ምግብ መምህር እና ተመራማሪ አቶ አምባ ጩፋ እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው የገዛቸው ዘመናዊ የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ተማሪዎች የሚማሩት ትምህርት በተግባር የተደገፈ እንዲሆን የሚያስችሉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው መምህርና የግብርና ኮሌጁ ዲን አቶ ግርማ ዳዊት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖችን በ30 ሚሊዮን ብር መግዛቱን ገልፀዋል፡፡
ማሽኖቹ ተማሪዎች በተግባር ትምህርታቸውን እንዲማሩ ከማስቻላቸውም በተጨማሪ በግቢ ውስጥ ላሉ የተሻሻሉ የወተት ላሞችና የቦረና ጊደሮች እንዲሁም በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ላቀደው የዓሳ እርባታ ስራ መኖ እያቀነባበሩ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል፡፡
የኮሌጁ ዲን፤ ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው ለተሻሻሉ የወተት ላሞች አንድ ኩንታል የተቀነባበረ መኖ ለመግዛት የሚያወጣውን አምስት ሺ ብር እንደሚያስቀርና ማቀነባበሪያ ማሽኖቹ ለዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ወሰኑ ዶይዴ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ