ሀዋሳ፡ መስከረም 25/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
ክልልሉ ከተመሰረተ በኃላ የመጀመሪያውን የትምህርት ጉባኤ “የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል ነው በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ እየተካሄደ ያለው።
በዕለቱም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ2017 ዕቅድ ይቀርባል።
በዕለቱ የቅድመ አንደኛ ትምህርትና የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች ዕቅድ ቀርቦ ይመከርበታል።
የክልሉ መምህራን ማህበር ሪፖርት የ2016 ዓ.ም ክልላዊና አገር አቀፋዊ የፈተና ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች በሴክቶሪያል ጉባኤው ውይይት ይደረግባቸዋል።
በመድረኩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ም/ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው አንተነህ ፈቃዱ እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል፡፡
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ