ሀዋሳ፡ መስከረም 25/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኣሪ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት ዋና ዋና ግቦች ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩም በ2017 የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር የበለጠ መስራት እንደሚጠበቅም ተመላክቷል
የኣሪ ዞን እራሱን ችሎ ከወጣ አንድ ዓመት ቢሆንም እቅዱን ለማሳካት በርካታ ተግዳሮቶችን በተቻለ መጠን እየፈታ ካቀዳቸው ዕቅዶች 86 በመቶ በመፈጸም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ደመላሽ አቦነህ ገልጸዋል፡፡
በማይክሮ ኢኮኖሚ የበጀት ቀመር መረጃዎችን አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል የሚያደርስና የፕሮጀክት ስራዎችን የሚሰራ ተቋም መሆኑን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡
በውይይቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠልና ደካማ ጎኖችን በማሻሻል የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም ልይ ትኩረት በመስጠት ለመስራት መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡
በስነ-ህዝብ ዘርፍም የ7 ዓመት መሪ ዕቅድ መዘጋጀቱን የገለጹት ሀላፊው እንደዞንም ኢኮኖሚው ከህዝብ ምጣኔ ጋር የተነጻጸረ እንዲሆን በስነ-ህዝብ ዘርፍ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የሶሺዮ ኢኮኖሚ መረጃዎችን በማደራጀት ሰፊ ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል አቶ ተሾመ ደበበ፤ አቶ ደጀኔ ጋንማይ፤ አቶ አንተነህ ሳልልህ፤ ወ/ሮ ውብአለም ተስፋዬ እንደገለጹት መድረኩ መዘጋጀቱ የሚበረታታ እንደሆነና ሌሎች የወረዳ ተቋማትም ቢሳተፉና ከቁልፍ አመራሮች ጀምሮ እስከ አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተው በተለይ በወረዳ መዋቅር ደረጃ የሚታየውን የሰው ሀይል እጥረት በአፋጣኝ ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ የሺእመቤት ዋሴ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ