ሀዋሳ፡ መስከረም 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2016 በጀት አመት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ 32 ባለሀብቶች ፈቃድ መሠጡትና ለ 3 ሺህ 827 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የጋሞ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ።
በ2017 በጀት አመት 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 26 ባለሀብቶች ፈቃድ ለመስጠት ግብ መጣሉም ተጠቅሷል።
የጋሞ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ግርማ ዞኑ ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኑ ባለፈው በጀት አመት በግብርና፣ በአገልግሎትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ 32 አልሚ ባለሀብቶች ፈቃድ የተሠጣቸው ሲሆን 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ካፒታል እንዳስመዘገቡ ተናግረዋል።
ባለሀብቶቹ የተፈጠረላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለ 3 ሺህ 827 ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሳሙኤል ለ 682 የአካባቢው ህብረተሰብ የቴክኖሎጂን ማሸጋገር መቻሉንም አክለዋል።
አያይዘውም ሁሉም ፕሮጀክቶች በየጊዜው ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው ሲሆን በገቡት ውል መሠረት ያላለሙ የግብርናና የአገልግሎት በአጠቃላይ አራት ፕሮጀክቶች የተሰረዙ ሲሆን አርባ አንድ ፕሮጀክቶች ማስጠንቀቅያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ አልፎ አልፎ መስተዋሉ አንዳንድ ባለሀብቶች በገቡት ውል መሠረት አለማልማት፣ ቋሚ የሰው ሀይል አለመቅጠር ችግሮች መስተዋላቸውን ጠቅሰው ሙሉ በሙሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል።
በ2017 በጀት አመት 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 26 የግብርና የአግልግሎትና የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ይሰጣቸዋል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ለ1 ሺህ 700 ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለ674 የአካባቢው ህብረተሰብ የቴክኖሎጂ ሽግግር ይደረጋል ተብሎ ይጠቃል ብለዋል አቶ ሳሙኤል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ