ሀዋሳ፡ መስከረም 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክረምት በጎ ፍቃድ ተግባራት በበጋ ወራትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኞና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል እንደሀገር የተጀመረውን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የሁለት አቅመ ደካማዎች ቤት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ ገርተጵና ጤናዳም ቀበሌ አካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኞና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ የክረምት በጎ ተግባር እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ያለ እንደመሆኑ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ሰው ተኮር የሆኑ ሥራዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተሠሩ በመሆናቸው ይህም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ሥራ ከግንባታው ባሻገር ሁለቱን ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ አስፈላጊ የቤት ቁሳቁሶችን በማሟላት ለአቅመ ደካማዎች እንደሚያስረክቡ ገልፀው አጠቃላይ ወጪውም 400 ሺህ ብር እንደሚፈጅ ገልፀዋል።
የኣሪ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታፈሰ ተሰፋዬ የክልሉ ሰራተኞና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ላደረገው ድጋፍ አመሰግነው አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ተፈፃሚ እንድሆን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የክልል ሰራተኞና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በክልሉ አቅመ ደካማዎችን በመደገፍ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልፀው ተግባሩ በበጋውም ወቅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የጤናዳም ቀበሌ አስተዳደር አቶ ጋልን ሐልሻይ ክልሉ ባደረገው ድጋፍ አመስግነው ለተጀመሩ የበጎ ተግባራት ሥራዎች የቅርብ ክትትል በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቁ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
ወ/ሮ አባይነሽ አንግሪ ወ/ሮ ቡዝነሽ ኡንጋ በጋራ እንደገለፁት ልጆቻችን በውትድርና ለሀገር መከላከያ ግዳጅ ላይ በመሆናቸው አጋዥ አጥተው እንደነበርና አሁን ላይ መንግስት ባደረገው የቤት ግንባታ ድጋፍ እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በተደረገው ድጋፍ ተቋሙን አመስግነዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ