ባለፉት ሶስት ወራት ከ111 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን ከ126 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱም ተመላክቷል።
የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙናዬ ሞሶሌ፤ የመምሪያውን የሶስት ወራት አፈጻጸም ሲገልጹ እንዳሉት በ2017 በጀት አመት አንደኛ ሩብ ዓመት 103 ሺ 210 የሀገር ውስጥና 8 ሺህ 371 የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን በዚህም 126 ሚሊዮን 337 ሺህ 521 ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 4 ነጥብ 5 ከመቶ የጎብኚዎች ልዩነት ሲኖረው የ5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የገቢ ብልጫ አንዳለውም ጠቅሰዋል።
ባለፈው በጀት አመት 397 ሺህ 446 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ዞኑን የጎበኙ ሲሆን 356 ሚሊዮን 553 ሺህ 459 ብር ገቢ መገኘቱንና በየአመቱ እድገት እያሳየ መምጣቱን አቶ ሙናዬ ተናግረዋል።
የዞኑ ሰላም መሆን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ዞኑን የማስተዋወቅ ስራ መሠራቱና ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መበራከት የቱሪስት ፍሰቱንና የገቢ አቅሙን ከፍ እንዳደረገው ጨምረው ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ