ሀዋሳ፡ መስከረም 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ “ዓመተ ልህቀት 2” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት ልህቀት በአንድ ጊዜ ስለማይመጣ ሀገሪቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
አምና አንድ ብለን ጀምረን አሁን ዓመተ ልህቀት ሁለት ላይ ደርሰናል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ለላቀ የሀገር ለውጥ ዘርፉን በማሳደግ ካደጉት ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ እንደሚሰራ አመላክተዋል።
መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች