መምሪያው “የግብዓት አቅርቦት ለትምህርት ስኬት ቀን” በሚል ቀኑን በማስመልከት በዞኑና በክልሉ ድጋፍ የተዘጋጀውን የተማሪዎች መጻህፍት ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍሌ በትምህርት ሳምንት የግብዓት ቀንን በማስመልከት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጽሐፍት ሥርጭት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመጽሀፍት አቅርቦት ለተማሪዎች ውጤት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት አቶ ዘማች፤ የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ በሚል ንቅናቄ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ርብርብ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር፣ በክልል ትምህርት ቢሮና በአንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ ዘመቻ በተሰበሰበ ሀብት የታተመው ከ197 ሺህ በላይ የመማሪያ መጻሕፍት መሰራጨታቸውን የገለጹት ኃላፊው በ2015 እና 2016 ዓ.ም ተሰራጭተው በትምህርት ቤቶች ያሉ መጻሐፍት ለተማሪዎች መከፋፈላቸውን አብራርተዋል፡፡
መጻሕፍቱ ከፍተኛ የመንግሥትና የህዝብ ገንዘብ ፈሶባቸው የታተሙ በመሆናቸው ሳይበላሹ ለትውልድ እንዲቆዩ በጥንቃቄ ለመያዝ ሁሉም ባለድርሻዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሸፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ