በዞኑ የአረም ቁጥጥር ሥራም እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በኮሬ ዞን ከ65 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በሰብል የተሸፈነ ሲሆን ለጤፍ ምርት ሰፊ ሽፋን መሰጠቱ ተመላክቷል።
በዞኑ በ2017 የምርት ዘመን የመኸር እርሻ በኩታገጠም የታረሰው ሰብል ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የግብርና መምሪያ ኃላፊና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ አስታውቀዋል።
የመካናይዜሽን ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት አቶ አስታረቀኝ፤ ከ20 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በኩታገጠም መታረሱን እንዲሁም የተባይ ቁጥጥርና የአረም ተግባርም በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።
አክለውም አርሶ አደሮች በጊዜው አረምን እንዲቆጣጠሩና በማሳቸው ውስጥ እርጥበትን የሚያቆዩበትን ዘዴ እንዲጠቀሙ ጠቁመዋል።
ከዞኑ ካነጋገርናቸው መካከል ሞዴል አርሶአደር ኤልያስ ይልማ ወቅቱን ጠብቀው በትራክተር ወደ 3 ሄክታር አሳርሰው የዘሩት ጤፍ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና የጉልበት ሠራተኞችን በማስተባበር አረምን የመቆጣጠር ተግባር እያከናወኑ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት።
አርሶ አደር ኮምፓስ አለኬ የአቶ ኤልያስ ጎረቤት ሲሆኑ ከዚህ በፊት በበሬ ሲያርሱ ወቅቱን ከመጠበቅና ምርትን ከማሳደግ አንፃር ብዙም ተጠቃሚ እንዳልነበሩ በመግለጽ በጎረቤታቸው ተሞክሮ በትራክተር በስፋት አርሰው በማረም የተሻለ ምርት አንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።