ሀዋሳ፡ መስከረም 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የስልጤ ዞን አስተዳደር ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምሁራን የምክክር መድረክ “የምሁራን ሚና ለህብረተሰብ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በወረቤ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በውይይት መድረኩ ምሁራን፣ የእምነት አባቶች፣ የዞን እና የወረዳ ባለድርሻ አካላትና ተጋበዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ እንኳን ደህና መጣችሁ መልክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፤ የዞኑን ህዝብ ልማት፣ እድገትና ባህል በማጎልበት ረገድ በምክንያታዊ ሀሳብ በማገዝ እና በጋራ በመስራት ምሁራን የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ: ሳጂዳ ሙዳስር – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ