የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቡቶ አኒቶ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ይሁን አሰፋ፣ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የብሄረሰቡ ተወላጆች በተገኙበት የየም ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በመከበር ላይ ነው።
የሄቦ በዓል ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሻገሪያና በጉጉት የሚጠበቅ በዓል ሲሆን በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው እርቀው የሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ታላቅ በዓል መሆኑ ይገለፃል።
ዘጋቢ: ፋሲል ኃይሉ
More Stories
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ
በኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የሥራ ጉብኝት አደረጉ
በህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነት እና ትብብር በልማቱ እና በሰላሙ ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ