ለሠራተኞች ጠንካራ የሥራ ባህልና ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር ይገባል ሲልም ቢሮው አመልክቷል ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ ለስራ ፈላጊ ዜጎች በሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር የስራ ዕድል እንዲፈጠር ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
ማህረሰብን መሠረት ያደረገ የማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የሚናገሩት የቢሮው ኃላፊ በዚህም ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የሀገር ውስጥና የውጪ የስራ ዕድል እንዲመቻችላቸውም ተደርጓልም ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ቤሔረሰቦች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳኤ በበኩላቸው በክልሉ የሠራተኛና አሠሪዎች እንቅስቃሴ ትርጉም ባለው መልኩ ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር በስልጠና ላይ መሠረት ያደረገ ስራ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በክልሉ በሰፊው የሚስተዋል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ባለድርሻ አካላት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን ሊያግዙ ይገባልም ብለዋል።
በይበልጥ ህጋዊ የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪትን ተግባራዊ በማድረግ ከስራ እድል ፈጠራ በተጨማሪ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከልም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አመላክተዋል።
ህገ ወጥ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አሁንም በክልሉ በሰፊው የሚስተዋል ነው ያሉት አቶ አዳማ የህብረተሰቡን ግንዛቤን በማሳደግ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ21 ሺህ 6 መቶ በላይ በክልሉ የሚገኙ ዜጎች በውጪ ሀገራት የስራ ዕድል እንዲያገኙ መደረጉም ከቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የቢሮው የ2016 በጀት አመት አፈፃፀምና የ2017 እቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
ዘጋቢ : በኃይሉ ሙሉጌታ
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ