ሀዋሳ፡ መስከረም 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ በዘርፉ የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ፡፡
የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች የትምህርት ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በዲላ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደትን ምልከታ አድርገዋል፡፡
ምልከታው ” ትምህርት ለሁሉም ” የትምህርት ሳምንትን ምክንያትን በማድረግ የተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል።
በተደረገው ምልከታ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳደር ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ፤ በትምህርት ሥራ የተፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት የቅርብ ክትትል በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ በትምህርት ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆናቸውን የገለጹት አስተዳዳሪው፥ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ለዚህም የዘርፉ አመራር አካላት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ አቋም በመውሰድ ለእቅዱ መሳካት የድርሻውን ሊወጡ እንደሚገባም ዶክተር ዝናቡ አሳስበዋል።
በቀጣይ ጥቂት ጊዜያትም ህብረተሰቡን በተለያዩ እርከኖች በማወያየት የተያዘውን እቅድ በማሳካት ትምህርትን ለበርካቶች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ከከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በምልከታ መርሃ ግብር የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ የከተማው አመራሮችና የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
የትምህርት ጥራት በማስጠበቅ በዘርፉ የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

More Stories
በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚባክነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን ጥምር ደን መጠበቅ፣ ማስፋትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማዘመን የዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ