የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ኢያሱ ኢትሳ እና የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በአሌ ዞን ኮላንጎ ከተማ በመገኘት አስተዳደር ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀምረዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል የቢሮ ኃላፊና ተወካይ አቶ ኢሳያስ ቢፍቱ ቢሮው በየአመቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት እየገነባ መቆየቱን ገልፀዋል ።
አሁንም በአሌ ዞን ኮላንጎ ከተማ አስተዳደር በመገኘት በ45 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ደረጃውን የጠበቀ የመኖሩያ ቤት ግንባታ ማስጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የበጎ ተግባር ስራ ከህሊና እርካታ ባለፈ በፈጣሪ ዘንድም ጽድቅ በመሆኑ እርስ በእርስ መደጋገፋችንን አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል ፡፡
የአሌ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ እያሱ ኢትሳ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ላደረገው በጎ ተግባር በዞኑ ስም አመስግነዋል፡፡
ባለቤታቸውን በሞት ያጡት እና የ5 ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ አስቴር መገርሳ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው ቢሮው ላረደገው በጎ ተግባር አመስግነዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን- ከአርባ ምንጭ
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ