በከተማው ካነጋገርናቸው ሴቶች መካከል ወ/ሮ እጅጋየሁ ይማምና ብርቱካን አወቀ እንደተናገሩት በተለይም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ብሎም የራሳቸውንና የልጆቻቸውን ጤና ለመጠበቅ በልማት ሕብረት ተደራጅተው በመስራት ውጤታማ መሆን መቻላቸውን ነው የገለጹት።
ቀደም ሲል ከነበረባቸውን የጠባቂነትና የተረጅነት ስሜት በመላቀቅና በሌማት ትሩፋት ዘርፍ በትጋት ሠርተው ኢኮኖሚያቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ጠቁመዋል።
በልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት በመስራት የጓሮ አትክልቶችን ካሮት፣ ሰላጣ፣ ቀይሰር፣ አበባ ጓመንና የመሳሰሉትን በማልማት ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶች ለቀጣይም ተለዋጭ ቦታቸውን ለማልማት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስረድተዋል።
የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ጽህፈት ቤት የሴቶች ሊግ ሀላፊ ወ/ሮ አማረች ኦብሴ በ2016 ዓ.ም ከ800 በላይ ሴቶች ወደ ስራ መግባታቸውንና ውጤታማ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በተለይም ከተማ አሰተዳደሩ ለችግኝ ግዥ 250 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረጉና ቦታ በማዘጋጀቱ ሴቶች ‹‹ምግቤን ከጓሮዬ ጤናዬን ከደጄ›› በሚል ከምግብነትም አልፎ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አስረድተዋል።
የይርጋጨፌ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ደንቢ ሴቶቸ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰሩ መሆናቸውንና በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።
ዘጋቢ ፡ ጽጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ