አቅመ ደካሞችን በመርዳት እና በመተጋገዝ በአብሮነት መስራት እንደሚገባ ቢሮው ገልጿል፡፡
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
የዱቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ኢያሱ ኢትሳ እና የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በአሌ ዞን ኮላንጎ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመኖሪያ ቤት ግንባታ አካሄደ፡፡
በቦታው ተገኝተው የቤት ግንባታ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል የቢሮ ኃላፊና ተወካይ አቶ ኢሳያስ ቢፍቱ፤ ቢሮው በየአመቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት እየገነባ መቆየቱን ገልፀዋል።
አሁንም በአሌ ዞን ኮላንጎ ከተማ አስተዳደር በመገኘት በ45 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የበጎ ተግባር ስራ ከህሊና እርካታ ባለፈ በፈጣሪ ዘንድም ጽድቅ በመሆኑ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ ለኢትዮጵያ ከፍታ እንረባረብ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአሌ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ እያሱ ኢትሳ፤ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ላደረገው በጎ ተግባር በዞኑ ስም አመስግነዋል፡፡
ባለቤታቸውን በሞት ያጡት እና የ5 ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ አስቴር መገርሳ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው የክልሉን መንገዶች ባለስልጣን እና የማናጅመንት አባላትን አመስግነዋል፡፡
ለግንባታው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ተሟልተው መቅረባቸውም ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለፁ
እንደሀገር ካለንበት ችግሮች ወጥተን ዜጎች ተረጋግተው የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን ምክክሩ እንደሚያግዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ
የጂንካ ዩኒቨርስቲ ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ