ሀዋሳ፡ መስከረም 15/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉን ህዝብ ባህልና ቋንቋ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ፡፡
የጎፋና ኦይዳ ብሄረሰቦች ባህልና ቋንቋ ላይ የተዘጋጀ ስምፖዚየምና የመጽሐፍ ምረቃ በሳውላ ከተማ ተካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከጎፋ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር በጎፍኛ፣ በኦይድኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለሕትመት የበቃው መጽሐፉ፥ ተረቶችና፣ ምሳሌያዊ ንግግሮች አባባሎች እና እንቆቅልሾች ከገላጭ ምስሎች ጋር የተካተተ ነው።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በየዓመቱ የሚከበረው የጎፋ “ጋዜ” ማስቃላ እና የኦይዳ “ዮኦ” ማስቃላ በዓል የሁለቱም ብሔረሰቦች ቱባ ባህላዊ እሴቶች ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት ድንቅ ባህላዊ ኩነት መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የጎፋ እና ኦይዳ ብሔረሰብ ተረቶች፣ ምሳሌያዊ ንግግሮች እና እንቆቅልሾች እንዲጠና፣ እንዲታተምና በዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ እንዲታወቅ በማድረግ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ ኦይቻ ክልሉ የበርካታ ብሔርና ብሄረሰቦች መገኛ፤ ተፈጥሮኣዊና ሰዉ ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት፤ ሰፊና ምቹ የቱሪስት መደረሻ ያለዉ፤ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በዉብ ቀለም ደምቀዉ የሚገኙባት፤ ክልል መሆኑን ተናግረዋል።
ቢሮው የብሄረሶቦችን ቋንቋ ባህልና እሴት በመጠበቅ፤ በመንከባከብና በመሰነድ ቀጣዩ ትውልድ እንዲያነብ እንዲማርና እንዲመራመር ተግቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የስምፖዚየሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዞኑን ባህልና ቋንቋ በማልማትና በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
አጀንዳዎችን በማሰባሰብ የህዝቡ ጥያቄ በተገቢው እንዲመለስ የምክክሩ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ እንዳለው ተሳታፊዎች ገለፁ
እንደሀገር ካለንበት ችግሮች ወጥተን ዜጎች ተረጋግተው የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን ምክክሩ እንደሚያግዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊ አካል ጉዳተኞች ተናገሩ
የጂንካ ዩኒቨርስቲ ለኤሶል ልዩ አዳሪ ትምህርት የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ