የዞኑ አስተዳደር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሯል።
በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የዉሃ አካላት ብክለትን ለመከላከል በትብብር እንደሚሰራ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሳምሶን ግቅሺ ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም የድምፅ ብክለትን ለመከላከል በጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ጋልሺ በበኩላቸው በከተማው የቆሻሻ ማስወገጃዎችን በመለየት በዘርፉ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ከወራጅ ዉሃ ብክለት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ በየደረጃው አደረጃጀቶችን በማጠናከር እንደሚሰራም ከንቲባው ተናግረዋል።
በእምነት ተቋማትና በግለሰቦች አማካኝነት የድምፅ ብክለት እያየለ በመምጣቱ ሥርዓት ሊበጅለት እንደሚገባ ከንቲባው አመላክተዋል።
በኣሪ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ፅህፈት ቤት የአካባቢ ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ኑሬሳ መርኪና እንደገለፁት የአካባቢ ብክለት የሰው ልጆች በሚያከናዉኗቸዉ አንዳንድ ተግባራት ጋር ተያይዞ የሚከሰት በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
ከጂንካ ከተማ ነዋሪዎች መካከል መምህር ፋንታው እሸቱና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት የድምፅ እና የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ዳኜ ጥላሁን – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!