ሀዋሳ፡ መስከረም 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የከተማ መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዋኖ ዋኬና የአለም ባንክ ካንትሪ ዳይሬክተር ሚስተር ማርቲን ኦንችያ የተመራ ሉዑክ ለሥራ ጉዳይ ወደ ኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ ገብተዋል።
ሉዑካን ቡድኑ ጂንካ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የኣሪ ዞን አሰተዳደር ተወካይ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
በቆይታቸውም በጂንካ ከተማ በመንግስትና በአለም ባንክ ድጋፍ እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎችን ጉብኝትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት በማድረግ ቀጣይ ሥራ ዙርያ የጋራ መግባቢያ እንደሚደረግ ታውቋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ