የጉራጌ ዞን 7ኛው የመስቀል ፌስቲቫል በእኖር ወረዳ በጋህራድ ጀፎሮ ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የቅርስ ተመራማሪ ዳይሬክተር ደ/ር ታደሰ ሰለሞን ፌስቲቫሉ የተጀመሩ የጥናት ስራዎች ትልቅ ግብአት ለማግኘት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለማነቃቃት ባህልና እሴቱ ይበልጥ እንዲጠብቀው እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላል ብለዋል።
ባለስልጣኑም ከዞኑ ጋር ያለው ቅንጅት በማጠናከር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹን በማጥናት በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ኑሪ ከድር እንደገለጹት መስቀል በጉራጌ በርካታ የሀገርና የውጭ የቱሪስት አይን ማረፊያ በመሆኑ በዓሉ ለመታደም በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ስራ ወዳዱና ታታሪዎቹ ጉራጌዎች ቀዬ የሚተሙበት በዓል ሆኗል ብለዋል።
በዓሉ የተቸገሩ የሚረዱበት የተጣሉ የሚታረቁበት ሙዚቃ፣ቲአትር እና ስነ ጹሁፉም ጎልቶ የሚንጸባረቅበት እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት የሚፈጥር ታላቅ በአል እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በመሆኑም የመስቀል በዓል የአደባባይ በዓል ሆኖ በፌስቲቫል መልክ እንዲከበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በቅንጅት እንደሚሰራ አቶ ኑሪ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ በበኩላቸው የመስቀል በዓል ከሀይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ የአስተሳሰብ ለውጥ ፣የአዲስ እቅድ ጅማሮ ፣የስኬት መንደርደርያ ፣የጋብቻ እና የመብዛት ነጸብራቅ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም በአካባቢ ልማት ፣በግብርናና የንግድ ስራዎች የሚመክሩበት ወጣቶች በአባቶች የሚመረቁበት ፣አብሮነትን የሚንጸባረቅበት ነው ያሉት።
በመሆኑም የመስቀል በዓል የጉራጌ ማህበረሰብ ትውፊቱን የሚያሳይበትና ማህበራዊ መስተጋብሩን የሚያከናውንበት በመሆኑ ይበልጥ ማስተዋወቅ እና ማበልጸግ እንደሚገባ አቶ አበራ አስታውቀዋል።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሠረት አመርጋ እንዳሉት ጉራጌ በመስቀል በዓል ወቅት ከማብላት እና ከማጠጣት ጎን ለጎን ተፈጥሮዊ እና ባህላዊ የቱሪስት መዳረሻዎቹን ለማስጎብኘት እያስቻለ ነው ።
ቱሪስቶቹ በእንግድነት ከመቀበል እና በክብር ከመሳተናገድ ባለፈ የማህበረሰባችን ቱባ እሴቶች ለማስተዋወቅ አጋዥ መሆኑንም ወ/ሮ መሰረት ተናግረዋል።
በበዓሉ የተገኙት አካላት መካከል ጜታኩየ መለሰ እና እንዳሉት በርካታ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ክዋኔዎች የሚፈጸሙበት ሲሆን በአሉ ስናከብር የተቸገሩ በመርዳት ፣በመተሳሰብ የሚከበር በመሆኑ ፌስቲቫሉ መዘጋጀቱ እንዳስታቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ ፡ እንዳልካቸው ደሳለኝ- ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ