በትናንትናው ዕለት በሆሳዕና ከተማ በሀድይ ነፈራ የተከበረው የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓልም ማስታወሻነቱ ለሀንሳር ጋራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንደሆነም ተገልጿል።
ለሀንሳር ጋራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎ ነበር የሃዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል የአካባበር ስነ ስርዓቱ የተጀመረው
የሀድያ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶክተር በፈቃዱ ገብረሃና ሀንሳር ገራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በህይወት ዘመናቸው በአገራችን ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል መሰረት እንዲኖረው የሰሩና ለህዝቦች እኩልነት፣ፍትህና ነፃነት የቆሙ፣የህዝቦች የባህል የቋንቋና የማንነት መብት እንዲከበር የታገሉና ያታገሉ የሀገሪቱ እንቁ ፓለቲከኛና ምሁር እንደነበሩም አንስተዋል።
የሀድያን ህዝብ፣ የብሔሩን ወዳጆች፣በሀገር ውስጥና ውጭ የሚኖሩ የብሔሩን ተወላጆች በማስተባበር ሀንሳር ገራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስንና ስራቸውን የሚመጥን ለመታሰቢያቸው የሚሆን ቅርስ በሀድያ ዞን ውስጥ እንደሚሰራም አሳውቀዋል።
የሀንሰር ገራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የስጋ ወንድማቸው ጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የሀገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ሉአላዊነቷን ለማስከበር ከጠላት ጋር ላደረገው ዘመን ለማይሽረው ታላቅ ገድል በዞኑ በሆሳዕና ከተማ መሃል አደባባይ “የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መታሰቢያ አደባባይ”በሚል በስሙ ታሪካዊ ቅርስ መቀመጡ ይታወቃል።
ዘጋቢ ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ