ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሃዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል የአደባባይ አከባበር በሆሳዕና ከተማ በሀድይ ናፈራ እየተካሄደ ይገኛል።
በኢፌዲሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስተር ዴኤታ አቶ አስፋው አዛሉ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱርዝም ቢሮ የቢሮ ምክትል ኃላፊና የባህል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ፣ የሀድያ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዶክተር በፈቃዱ ገ/ሃና፣ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ እቴነሽ ሙሉጌታ፣ የባህል ሽመግሌዎች፣ ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የሆሳዕና ከተማና የሁሉም የዞኑ መዋቅር ነዋሪዎችና የብሔሩ ተወላጆች እየታደሙ ይገኛል።
የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት የተጀመረው ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለሀንሳር ጋራድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።
ዘጋቢ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች