በወረዳው የ2017 በጀት ዓመት የእንስሳት ዝሪያ ለማሻሻል ከብቶችን የማዳቀል ሥራ ተጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የተገኙ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ሚጁ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የእንስሳት ዝርያ ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት ጥሩ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የገቢ አቅምን ለማሳደግም አርሶ አደሩ ከወትሮው በበለጠ መልኩ ሥራውን እንዲያጠናክረው አሳስበዋል፡፡
ካነጋገርናቸው አርሶአደሮች መካከል ፍስሀ ገልገሉና ታምራት ካሳሁን እንደገለፁት ከግብርና ባለሙያዎች ባገኙት ግንዛቤ የተሻሻሉ የወተት ከብቶችን በማርባት ገቢያቸውን እያሳደጉ ነው፡፡
እንደ ይርጋጨፌ ወረዳ ከ45 ሺህ በላይ ከብቶች እንዳሉ ያስታወቁት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍለ ጅግሶ ከብዛት ይልቅ በጥራት ላይ በመስራት የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከወተት የሚገኙውን ጠቀመታ በመረዳት ሁሉም በዘርፉ በትኩረት እንዲሰራ የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ምክትልና እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምራት ክጶ አሳስበዋል፡፡
የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሀገረሰብ ከብቶችን በተሻሻለው ዝሪያ መለወጥ፣ የተሻሻለ የመኖ ዝሪያ ማልማትና መጠቀም እንዲሁም የእንስሳት ጤና መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት የጌዴኦ ዞን ግብር መምሪያ ምክትልና የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቢንያም ማሪዮ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት ተግባራት የወተት ምርትና ምርታማነት እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ