የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የድጋፋዊ ክትትል ቡድን በጌዴኦ ዞን ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡
የፓርቲው ድጋፍና ክትትል ቡድን በዞኑ የተከናወኑ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራት እየተመራ ያለበትን ሂደት በመገምገም ቀሪ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡
በትምህርት ሥራ አጀማመር፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ፣ የእሸት ቡና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች፣ የ15 ቀናት የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫዎችና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ተግባራት ለመድረኩ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መነሻ አስተያየትና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳጌ ሻንሞባ፤ አመራሩ ቁርጠኛ በመሆንና ቅንጅት ፈጥሮ በመስራቱ የሚታይ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የቀረበው ሪፖርት አበረታች መሆኑን የገለጹት ኃላፊው በትምህርት፣ በገቢና በሌሎች ዘርፎች የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሀብትና ልማት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ህዳቶ በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከር ለመጪው ትውልድ የሚቀር አሻራ ለማስቀመጥ መረባረብ አለብን ብለዋል
የድጋፍና ክትትል ቡድን አባልና የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ዮሴፍ ማሩ አካባቢውን ከብክለት ነጻ ለማድረግ የላስቲክ አወጋገድ በማጠናከር የአፈር ለምነት በመጠበቅና የወንዞችን ብክለት በመከላከል አረንጓዴ አካባቢ ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው ክልሉን ለማሻገር በሁሉም መዋቅሮች መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች