ሀዋሳ፡ መስከረም 07/2017 ዓ.ም የሳተላይት አካውንቱ መረጃዎችን ሰንዶ በማስቀመጥ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል ።
በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በተዘጋጀው በዚሁ የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ላይ የቱርዝም ሚኒስትር አምባሰደር ናሲሴ ጫሊ እንዳስታወቁት የሳታላይት አካውንት ዝግጅቱ በዋናነት ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ለሥራው ስኬታማነት ጉልህ አበርክቶ ያደረጉ ሌሎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችንም አመስግነዋል ።
የዓለም የቱሪዝም ቀን ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከዛሬ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይከበራል።
በዚሁ በዓልም የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከ100 በላይ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ጎን ለጎን የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ዓውደ ርዕይ በይፋ ተጀምሯል ።
በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በተዘጋጀው የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ለይ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የቱርዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሌሎች የአገር ውስጥ እና የወጪ አገር ዜጎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በከተማው የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ የተሰበሰበውን ሀብት በቁጠባና በግልጸኝነት መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ኮሌጆች በዕውቀትና ክህሎት የበለፀገ ትውልድ በማፍራት ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበርከት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ
በጎፋ ዞን ኢሲፔ ዲቻ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን ካፒታሉን 62 ሚሊየን ብር በማድረስ ዓመታዊ ትርፉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን አስታወቀ