የኬሌ ከተማ አስተዳደር ለአቅመ ደካሞችና ወላጅ አልባ ህፃናት የአልባሳትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የኬሌ ከተማ ዋና አፈ ጉባኤና የከተማው ከንቲባ ተወካይ ወ/ሮ ሃና ኃይሌ ድጋፍ የተደረገላቸው ተረጂዎች ጀርባ ሌሎች መኖራቸውን በማስታወስ ሁሉም ሰው የመረዳዳት ባህል ማጎልበት እንደሚገባው አስረድተዋል።

የድጋፉን ቁሳቁስ ያሰባሰቡት በኬሌ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የቀድሞ ኃላፊ ወ/ሮ ርብቃ ታዬ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ መሆኑን አስታውሰው ድጋፉን ያበረከቱ አካላትና ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ሰውተው ያገለገሉ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን አመስግነዋል።

በኬሌ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የወጣቶች ማካተትና ንቅናቄ ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ ዳግም ጀምቦ እንደገለጹት፤ የአልባሳትና የትምህርት ቁሳቁስ የተደረገው ለ1መቶ 20 በላይ አረጋውያን፣ ወላጅ ላጡና ለአደራ ልጆች ነው።

ዘጋቢ: ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን