ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ቅን ልብ ካላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ የሆኑት ማስተር አብነት፤ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያሳዩ የቁርጥ ቀን ልጃችን ናቸው ብለዋል።
ማስተር አብነት አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ክስተቱ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለምአቀፍ ደረጃ እንዲታወቅና ተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች በማሰራጨት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
ማስተር አብነት ለተጎጂዎች በራሳቸው ከሚያደርጓቸው ድጋፎች በተጨማሪ ኢትዮጵያውያንና በተለያዩ ዓለም ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ በማስተባበር ላሳዩት ኢትዮጵያዊነት በዞኑ አስተዳደርና በተጎጂ ቤተሰቦች ስም ኢንጂነር ዳግማዊ አመስግነዋል።
በዕለቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት ከጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ እጅ ለማስተር አብነት ከበደ ተበርክቶላቸዋል።
ማስተር አብነት ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት፥ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ ዜጎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸው፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበኩላቸውን ድርሻ ሲወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይ ተጎጂዎች በዘላቂነት እስኪቋቋሙ ድረስ የሚያደርጉትን ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማስተር አብነት ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ
በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ