የሳውላ ደምባ ጎፋ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ መሐመድ ሲረጅ ህዝበ ሙስሊሙ 1ሺ 499ኛውን የመውሊድ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን ወገኖችን ከማብላትና ከማጠጣት ባለፈ የሀገር ሠላምና አንድነት እንዲጠናከር ዱዓ በማድረግ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
በአሉ በእስልምና አስተምህሮ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውን ነብዩ ሙሀመድ የተወለዱበትን ዕለትና ለሰው ልጆች ያስተማሩትን መልካምና በጎ ስራ ለመዘከር ታስቦ እንደሚከበር ገልጸዋል።
የሳውላ ፈትህ መስጅድ የሞሊድ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መሐመድ ኢብራሂም በበኩላቸው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል ለአለማት እዝነት እና ሰላም ተደርጎ ወደዚች ምድር የመጡበት ዕለት በመሆኑ የደስታና የመተሳሰብ ቀን መሆኑን ተናግረዋል።
የመውሊድ በዓልን ስናከብር የነብዩ መሐመድን አስተምህሮትን በመከተል ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ካነጋገርናቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ መሐመድ አህመድ፣ ወ/ሮ ሶፊያ የሱፍ እና ወ/ሮ ሶፊያ በድሩ ከታላቁ ነብይ መልካም ስብዕናን፣ ለሰው አሳቢነትና ርህራሄ የምናስታውስበት በመሆኑ የእሳቸውን ክብርና ሀቅ በጠበቀ መልኩ ቀኑን ማሳለፋቸውን ተናግረዋል
ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የእሳቸውን መልካምነት በመላበስ የተቸገሩትን በመርዳት፣ ሰላም፣ ፍቅርና እዝነትን በተግባር በማሳየት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን- ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ