በይርጋጨፌ ከተማ የኑሪ መስጂድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሳበሀ አለሙ 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ መከበሩን ገልጸው ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞችና ለጎዳና ተዳዳሪዎች የማዕድ ምገባ ሥነ ስርዓት መከናወኑንም አክለዋል፡፡
በህዝበ ሙስሊሙ መካከል የቆየው አንድነትና ሠላም ተጠናክሮ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ሳበሀ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አቶ ሰዒድ አሊና ወ/ሮ ሙውባ ደልታታ ህዝቤ ሙስሊ አቅመ ደካሞችን የተቸገሩት በመርዳት በዓሉን እንደሚያከብሩ ተናግረዋል፡፡
ወጣት ጃፈር መሀመድና ጓደኞቹ 1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ ምክንያት በማድረግ በበጎ ሥራ ተሰማርተው አባቶችን በማገዝ፣ እርድ በማከናወን በምገባ ሥራ መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ተናገሩ
በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ ያለውን የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራ በታቀደው ጊዜ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ