የመውሊድ በዓል ሲከበር በጎ ነገር በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ የሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች መካከል ካነጋገርናቸው የእስለምና እምነት ተከታዬች መካከል አህመድ አባፊጣ እና መሀመድ አባፊጣ እንደተናገሩት በዓሉ ሲከበር ነብዩ መሀመድ (ሱ.ዓ.ወ) በህይወት ዘመናቸው ያከናወኗቸውን መልካም ተግባራቶችን በማውሳትና የርሳቸውን ታሪክ በማንሳትና በማወደስ ለሌሎች ትምህርት እንዲሆን በደመቀ ሁኔታ እነደሚያከብሩ ተናግረዋል።

አቶ ጅፋር አባፊጣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል የእስልምና ጉዳይ ተቀዳሚ ም/ል ፕረዝደንት እና የኮንታ ዞን የእስልምና ተወካይ ህዝበ ሙስሊሙ 1ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማልበስም ጭምር መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

በአሉ በእስልምና አስተምህሮት መሰረት ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸውን ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱበትን ዕለት ለማሰብና እርሳቸው ለትውልድ ሁሉ ያስተማሩትን እና ያስተላለፉትን መልካምና በጎ ስራ ለመዘከርና ለማወደስ ታስቦ ዕለቱ እንደሚከበር ገልጸዋል።

ዘጋቢ: ፋሲካ ሙሉጌታ – ከዋካ ጣቢያች