ሀዋሳ፡ መስከረም 02/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና ለህግ ታራሚዎች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሄደ፡፡
የኬሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ዮሐንስ ኃይሉ፣ ማዕድ ማጋራት በህብረተሰቡ ዘንድ የተለመደ መሆኑን በመግለጽ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኮሬ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳግም ታደሰ በበኩላቸው ማዕድ ማጋራት የአብሮነት መገለጫ መሆኑን አብራርተዋል።
የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም የተዘጋጀው 4 መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች፣ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጅ ላጡ ህፃናትና ለህግ ታራሚዎች መሆኑን የተናገሩት የኬሌ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ርብቃ ታየ ናቸው።
የድጋፉ ገንዘብ የተገኘው ከኮሬ ዞን፣ ከከተማው አስተዳደርና አመራሮች ሲሆን የከተማው በጎ አድራጊ ወጣቶች በጉልበታቸው አስተዋጽኦ አድረገዋል ብለዋል ወ/ሮ ርብቃ።
ዘጋቢ: ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና አርባምንጭ ከተማን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በንቃት በመሳተፍ የሚፈልገውን መንግስት ለመምረጥ መዘጋጀት እንዳለበት ተገለጸ
ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል