የህይወት ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ የቅርጫ ስጋ ድጋፍ አደረጉ

ሀዋሳ፡ መስከረም 02/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህይወት ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር የ2017 አዲስ አመት ዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የቅርጫ ስጋ በመስጠታቸው መደሰታቸዉን የማህበሩ አባላት ተናገሩ።

የህይወት ስንቅ በጎ አድራጎት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አለምሰገድ ዘካርያስና ጋሻውን ኃይሌ እንዳሉት በወረዳው ዋካ ከተማና አከባቢው አቅም ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፥ አሁንም በዓሉን ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው የቅርጫ በማዘጋጀት ለበዓል መዋያ የሚሆን ስጋ ማከፋፈላቸውን ተናግረዋል።

ወጣቶቹ በተለያዩ ዘርፎች አቅም የሌላቸውን ተጠቃሚ እያደረጉ መቆየታቸውን ጠቁመው፥ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌ ለአምስት አቅመ ደካሞች ቤት ሰርተው መስጠታቸውን አስረድተዋል። ይህንንም ተግባር በቀጣይም አጠናክረው እንደምቀጥሉ ጠቁመዋል። ወጣቶቹ ለዝሁ ተግባር አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ አመስግነው፥ ይህም ቀጣይነት እንዲኖረው ሌሎች ፍቃደኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችም ለማህበሩ መጠናከር የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወ/ሮ ተዘራሽ ታደሰ አልማዝ አየለና አቶ ዳሮታ ዳወና የወጣቶቹ ተግባር በአሉን በሐዘን ከማሳለፍ እንደታደጋቸዉ ተናግረዋል። በዚህም በአሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ላደረጉት ወጣቶች መልካሙን ተመኝተውላቸዋል።

በዕለቱ በቦታው ተገኝቸዉ ወጣቶችን ያበረታቱት ቄስ ሉቃስ ጌታቸውና ፓስተር ጴጥሮስ ኡታ የወጣቶች ተግባር አርዓያነት ያለው ክርስትያናዊ ተግባር መሆኑን ጠቁመው፥ እንዲህ አይነቱ ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበው እነሱም የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የወረዳዉ ምትክል አስተዳዳርና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ብልጽግና ፓርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ኦርሳና አልታየና ዘካርያስ ወንድሙ ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ወረዳው መንግስት የወጣቶች ተግባር ለሌሎች ወጣቶች ተምሳሌት የሚሆን ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። የወረዳው መንግስት በተቻላቸው መጠን የወጣቶቹ ተግባርም ተጠናክሮ እንድቀጥል እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።

 ዘጋቢ፡ እሸቱ ወርቅነህ – ከዋካ ጣቢያችን