መሥሪያ ቤቱ ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት ግንባታና ለወላጅ አጥ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የላስካ ከተማ ከንቲባ ምልኪያስ ዶሮ በከተማ አስተዳደሩ በክረምትና በጋ የበጎ ስራዎች የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው የበጎነት ተግባር ስራም ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
በዞኑ በርካታ ቤቶችን ገንብቶ ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን ማስረከብ መቻሉን የተናገሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፍሬው ፍሻለው የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትም ሙሉ ወጪ ሸፍኖ ለሚያደርገው የአቅመ ደካማ አረጋዊት ቤት ግንባታ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ኦዲተር መሠሪያ ዋና ኦዲተር አበባዬሁ ኤርምያስ ባሳለፍነው 2016 ዓ.ም እንደ ክልል የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በርካታ ለውጦች ማስመገዝብ የቻለበት መሆኑን ገልጸዋል።
በጎነት ድንበር የለሽ ተግባር በመሆኑ መደጋገፍና መረዳዳት የዘውትር ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸው መሥሪያ ቤቱ የጀመረውን የቤት ግንባታ ሙሉ ወጪውን ችሎ በአጭር ግዜ እንደሚያስረክብ ቃል ገብተዋል።
መሥራያ ቤቱ ለወላጅ አጥ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዋና ኦዲተር አቶ አበባዬሁ ኤርምያስ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ:- አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማጠናከር ክልላዊ አንድነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ