የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ የመድረኩን ዓላማ ሲገልጹ ተስፋ ያላት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስረከብን እንደሆነ በመግለጽ ወጣቱ በኃላፊነት ስሜት የነገ ሀገር እንዲረከብ ጠይቀዋል።
በመድረኩም በዛሬው ቀን የቀረቡ ወጣቶች ኃላፊነት መሸከም የሚችል ወጣት ያለን መሆኑን አረጋግጠውልናል ብለዋል አቶ ንጋቱ ዳንሳ።
በጋራ አቋማችሁ አገር እንዲህ ናት የሚል መልዕክት አስተላልፋችኋል ያሉት የቢሮው ኃላፊ እጅ ለእጅ ተያይዘን የተጀመረውን ብልጽግና የምናስቀጥልበት ይሁን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዳንኤል ደሌ ጳጉሜን 5 የነገ ቀን ከዛሬው ፕሮግራም ዝግጅት ብዙ ተምረናል ሲሉ በመግለጽ እኛ ከአባቶቻችን የተረከብናትን ውብ ሀገር ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር የምናስረክብበት ልጆች የማስቀጠል ኃላፊነት የሚረከቡበት ነው ብለዋል።
በመድረኩ በህጻናትና ወጣቶች የተዘጋጁ የተለያዩ ትርዕቶችና ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ከወላይታ ዞን ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት የተማሪ መጻህፍት ለወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ የማስረከብ እንዲሁም ለህጻናት ሰንደቅ ዓላማ የማስረከብ ሥነሥርዓት ተካሂዷል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ