ዛሬ ላይ ሆነን የነገውን ብልጽግና እውን ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አስታወቀ

ጳጉሜ 5 የነገ ቀን በሚል መሪ ቃል በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ተከብሯል፡፡

የዓመቱ የመጨረሻ ቀን ሆኖ በተከበረው “የነገ” ቀን ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ለነገ ኢትዮጵያ ብልጵግና አቅም እንዲሆን በማሰብ ዛሬ ላይ በርካታ የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ሥራና በዩኔስኮ የተመዘገበው የአካባቢው ምህዳር አጠባበቅ ሥርዓት የነገውን ብልጽግና እውን ለማድረግ ታሳቢ ተደርጎ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የነገውን ትውልድ ሊጠቅሙ የሚችሉ አሻራ የማሳረፍ ሥራ ከዳር እንዲደርስ ተግቶ መስራት የሚጠይቅ በመሆኑ በቡናና በሌሎች ዘርፎች የተጀመረው ሥራ መጠናከር እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡

በልዩ ልዩ መርሀ-ግብሮች እየተከበረ ባለው የነገ ቀን ላይ የተገኙ የተለያዩ የዲላ ክላስተር የቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞን ኃላፊዎች፣ የዲላ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በከተማው የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን