በሄኖክ አበራ
ተግባቦት||Communication ለሰው ልጅ መሰረታዊ ከሆኑ ክህሎቶች አንዱ ነው።
የተግባቦት ክህሎት የሚጎድለው ሰው ለመኖር ይቸገራል።
መኖር ከራስ, ከሌላ ሰው, ከእንስሳት, ከተፈጥሮ, ከብዙሃን, ከማህበረሰብ ጋር ያለ ተግባቦት የሚታሰብ አይደለም።
መጀመሪያ ግን ከማን ጋር እንግባባ? በኔ እይታ ብዙሃኑም እንደሚጋሩት አስቀድሞ ከራስ ጋር መግባባት ይጠቅማል።
ከተግባቦት( |Communication) አይነቶች አንድኛው Intrapersonal communication ነው።
ህልማችን , በዉስጣችን አሊያም ደግሞ ቃል አዉጥተን ለብቻችን የምናደርገው ንግግር , የምናስበው ሀሳብ , ማሰላሰል ወይንም አርምሞ የ Intrapersonal communication መገለጫዎች ናቸው።
ይህ ተግባቦት ስለራሳችን ያለንን ግንዛቤ እንድናሳድግ , የመወሰን አቅማችን እንዲሻሻል , ጭንቀትና ስጋት እንዲቀንስ እና በራስ መተማመን እንዲጨምር ያስችላል።
ከራሳቸው ጋር የመግባባት ክህሎት ያላቸው ከሌሎች ጋር ለመግባባት አይቸገሩም። ከራስ ጋር መጣላት ከሌላ ጋር ላለመግባባት ምክንያት ይሆናል። እናም መጀመሪያ ከራሳችን ጋር መግባባት ላይ ትኩረት ብናደርግ የተሳካ ተግባቦት ይኖረናል። ከዚያም ከሌሎች ጋር ለመግባባት አንቸገርም።
የ Interpersonal communication ክህሎት ጥቅሙ ብዙ ነው። ይህ ክህሎት መናገርን ማድመጥን እንዲሁም ጠሊቅ አሳቢነትን ያካትታል።
የራስን ፍላጎት በግልጽ ቋንቋ ለማስረዳት ከሌሎችም ጋር ዉጤታማ ግንኙነት ለማድረግ ይረዳል።
ጤናማ የሆነ የግል እና የሙያ ግንኙነት ለመመስረት ያግዛል።
በአጠቃላይ ከራሳችን አሊያም ከሌሎች ጋር የምኖረን ተግባቦት ውጤታማነት በግልም ሆነ በጋራ ህይወት በቤተሰብም ሆነ በስራ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
እናም በአዲስ ዓመት ከማን ጋር እንግባባ? ጥያቄ
ከሌሎች ለመግባባት ከራስ መግባባት ይቀድማልና የተግባቦት ስርዓታችን አካሄድ ከራስ መጀመር አለበት ብዬ አስባለሁ።
More Stories
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ